ይህ ፕሮጄክት ፣ ከተረጂነት ተላቅቀው ስራ ፈጣሪና አምራች በሆኑ ነዋሪዎቿ የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ተምሳሌት የሆነች ድሬዳዋን እውን ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አካል መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሒም ገልጸዋል፡፡
ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ አቅመ ደካሞች በቀጥታ ከሰባት ሺህ ስድስት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ በከተማ ጽዳትና ውበት ስራ የፕሮጄክቱ ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የከተማ ምግብ ዋስትና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም ሙደኔ ገልጸዋል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር በ1ኛው ዙር አርባ ሶስት ሺህ ፣ በሁለተኛው ስድስት ሺህ ሰዎችን በዚህ ፕሮጄክት ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን አሁን ይፋ በተደረገው የ2017 ዓ/ ም ሶስተኛ ዙር የከተማ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጄክት ዘጠኝ ሺህ ሰላሳ ሰባት ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በዳንኤል አማረ
ፎቶ ፡-ሰላም አበበ እና አገኘው ሸዋረጋ


