ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራባቸው ከሚገኙ ዘርፎች መካከል አንዱ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ ሲሆን “አፈራችን ለሀገራችን ብልፅግና”በሚል መሪ ቃል በቀለዓድ ክላስተር ለተከታታይ 30 ቀናት ሲከናወን የቆየው የ2017 ዓ.ም የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራም በእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር ተጠናቋል።
የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራ እንደሀገር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ያለ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ሲሆን በአስተዳደራችንም ለተከታታይ አመታት በህብረተሰብ ተሳትፎ በተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል።
በቀለዓድ ክላስተር 2017 ዓ.ም ሲከናወን የቆየው የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ማጠቃለያ መርሀ ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በገርባ አነኖ ቀበሌ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አካላት እውቅናና ሽልማት በመስጠት የተጠናቀቀ ሲሆን እንደ አስተዳደር ሲከናወን የቆየው የክረምት ወራት የተፋስስ ልማት ስራ በመንግስት እና በፓርቲ አመራሮች በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት እና በህብረተሰቡ የላቀ ተሳትፎ ውጤታማ ስራዎችን መስራት እንደተቻለና በዚህም በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ የተቻለ መሆኑም ነው የተገለፀው።
በመርሀ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ፣ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስትና የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና የክላስተሩ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።


