ኑሮውን በአሜሪካ ሀገር ያደረገውና በተለያዩ ጊዜያቶች አቅመ ደካማ ለሆኑ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ የሚታወቀው ዘኪ መሀመድ የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ 300 ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የምግብ ፍጆታዎችን በዛሬው እለት ድጋፍ ማድረግ ችሏል ።
በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ዘኪ መሀመድ ባለፈው አመትም መሰል ድጋፍ ማድረጉን አንስተው በዛሬው እለትም የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ 300 ለሚሆኑ ወገኖቻችን ድጋፍ በማድረጉ ምስጋናቸውን በእለቱ አቅርበዋል ።
ድሬዳዋ የፍቅር እና የአንድነት ከተማ መሆኗን የድሬደዋ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሰብሳቢ ሼክ ኢብራሂም ኢማም ተናግረው በተለይም ህዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በረመዳን ፆም ወር ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች አቅመ ደካማ የሆኑ ወገኖቻችንን መደገፍ እንደሚገባም ተናግረዋል ።
በረመዳን ፆም ወር ወቅት ያለው የሌለውን መርዳት እና ማገዝ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ካሊድ መሀመድ ተናግረው ወጣት ዘኪ መሀመድ በዛሬው እለት 300 ለሚሆኑ ወገኖቻችን የምግብ ፍጆታዎችን ድጋፍ በማድረጉም አቶ ካሊድ ምስጋናቸውን በእለቱ አቅርበዋል።
የድጋፍ አስተባባሪ የሆነው ወጣት ጃፈር አሚን በበኩሉ ዘኪ መሀመድ ለአቅመ ደካማ እና ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው ወገኖቻችን ባለፈው አመትም ከሁለት መቶ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ድጋፍ ማድረጉን ተናግሮ በዛሬው እለትም 300 ለሚሆኑ ወገኖቻችን የምግብ ምጆታዎች ድጋፍ ማድረጉንም ተናግሯል ።
በአለማየሁ አበበ
ፎቶ :- አገኘው ሸዋረጋ


