የካብኔ ውሳኔዋች

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ትላት ጠዋት ባካሄደው ስብሰባ ውሳኔ አስተላልፉል

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮችን ተመልክቶ ውሳኔዎችን አሰተላልፏል፦

1ኛ :- በአስተዳደሩ እየተሰሩ ለሚገኙ የልማት ኘሮጀክቶች በወረዳ 1 የመልካ ጀብዱ የልማት ተነሺዋች አካባቢያቸውን አፅድተው ለመንግስት በማስረከብ ለልማቱ ያላቸውን ተነሳሽነት እና የካሳ ክፍያውን በትዕግስት በመጠበቅ ላሳዩት ቀና ትብብር በአስተዳደሩ ስም ምስጋና በማቅረብ ከመጋቢት 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ በከንቲባ ጽ/ቤት በካሳ ክፍያና መልሶ ማቋቋም ቅሬታ አፈታት ዳይሬክቶሬት ቀርበው የካሳ ግምታቸውን እንዲወስዱ ውሳኔ አሰተላልፉል።

2ኛ:- የፌደራል ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር ትልቁን ሁለተኛ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለመክፈት ባቀረበው የግንባታ ቦታ ጥያቄ ላይ ካብኔው ተወያይቶ መፈቀዱን ውሳኔ አሳልፉል።

3ኛ ፦የንግዱን ቀጠና ከነፃ የንግድ ቀጠናው ዞን ጋር ለማሳለጥ የከባድ ጭነት መኪና ማቆሚያ ቦታ ችግር ለመቅረፍ በነፃ የንግድ ቀጠና አካባቢ የማቆሚያ ቦታ ግንባታ እንዲገነባ ውሳኔ አሳልፋል

4ኛ, በዲፖ፣በገንደቆሬ እና ቦረን አካባቢ NDP ኘሮግራም በተጠና ጥናት ማሻሻያ ላይ ካብኔው ተወያይቶ አፅድቆታል።

5,ቀደም ሲል በገጠር በግብርና እና ውሀ መአድን ኢነርጂ ቢሮ በከተማ በስራ ከህሎት አና ቴክኖሎጂ ቢሮ ለወጣቱ የስራ እድል ለመፍጠር ስራዋች እየተሰሩ ቢሆንም የተገኘው ውጤት አበረታች ባለመሆኑ በቀጣይ በስራ ከህሎት አና ቴክኖሎጂ ቢሮ ስር እራሱን የቻለ የስራ ዕድል ጽ/ቤት በአዲስ እንዲዋቀር የውሳኔ አሳልፋል።

6ኛ፦በቀጣይ ከመሬት ጋር በተያያዘ አስተዳደሩ ከስር ከስር እንደሚፈታ ተወያይተው ውሳኔዋችን አስተላልፉል

የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *