#DGC መጋቢት 16/2017
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ አርአያነቱን ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትም ሊከተሉት እንደሚገባቸው ገልጸዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት እና ስኬት እያበረከተ ካለው አስተዋጾና አገልግሎት ባሻገር ከሚያገኘው ትርፍ ላይ እና ሰራተኞቹን በማስተባበር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚያደርጋቸው ተግባራት መካከከል ይህ በድሬዳዋ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች “አብሮነት ለበጎነት “ በሚል መሪ ሐሳብ የተደረገው የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ፣ በምእራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማም እንደዚሁ ለአንድ መቶ ሃምሳ ሰዎች በድምሩ ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማደረግ ተመሳሳይ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ያደረገው ይህ የምግብ ፍጆታ ስጦታ ፣እንደ ሀገር መንግስት ሰው ተኮር ተግባራት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የግልና የመንግስት ተቋማትን በማስተባበር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እያደረገ ያለው የበጎነት ስራ አንድ አካል ነው ያሉት የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሐመድ ፣ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመጣት እያደረገ ያለውን አርአያነት ሌሎች የፋይናንስ ተቋማትም ሊከተሉት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲህ ያለውን የምግብ ፍጆታ ስጦታ ባፈውም ዓመት ማድረጉን አስታውሰው ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በኩል በቅርቡ ለሜቄዶኒያ የአረጋዊያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ህንጻ ማሰሪያ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሰራተኞቹን በማስባበር ሰላሳ ሚሊየን ብር መለገሱን ጠቅሰው ወደፊትም መሰል ተሳትፎዎችን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የገለጹት የድሬዳዋ ዲስትሪክት የሲቢኢ ኑር ዳይሬክተር አቶ ታጁዲን ኡመር ናቸው ፡፡
ደጋፉ የተበረከተላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ባንኩ ላደረገው የምግብ ፍጆታ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በክርስትናና የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተጾሙ የሚገኙ አጽዋማትን መነሻ በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ አንድ መቶ ሃምሳ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ያደረገውን የምግብ ድጋፍ የድሬዳዋ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲያ አደን ፣ የደሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የተከበሩ አቶ አርቢ ቡህ፣የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሐመድ እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ በቃና በስፍራው ተገኝተው አበርክተዋል፡፡
በዳንኤል አማረ
ምስል ዳዊት


