የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

#DGC መጋቢት 15/2017

“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ የወጣቶች ሚናን በተመለከተ በድሬዳዋ አስተዳደር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረው፤ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴና የዋና ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ገዛከኝ አንዳርጌ በበኩላቸው የወጣቶችን ተጠቃሚነት አበርክቶና ተሳትፎ ለማረጋገጥ የብልፅግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ አቅጣጫ መቀመጡን በመግለፅ፤ የወጣቶች አደረጃጀትን በመያዝ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም አመላክተዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አደረጃጀት የፓርቲውን መሰረታዊ እሳቤ አምነው የተቀበሉ ወጣቶችን አቅፎ ለሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውና የላቀ ተሳትፎ የሚታገልና የሚያታግል ክንፍ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የወጣት ክንፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሔይዲን አብዱረህማን ናቸው።

በመድረኩ ሲሳተፉ ያነጋገርናቸው ወጣቶች በበኩላቸው ሀገራችን የጀመረችውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማፋጠን የበኩላችንን ሚና ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ ገልፀዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *