በመርሀ ግብሩ ላይ በመንገድ ትራፊክ አደጋና በተለያዩ ምክንያት በሆስፒታል አልጋ ላሉ ወገኖች የገንዘብ እና አይነት ድጋፍ ተደርጓል።
በመርሀግብሩ ላይ በመገኘት ድጋፋን ከተለያዩ እንግዶች ጋር ያስረከቡት በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርጫፍ ፅ/ፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደረጃ ፀጋዬ ብልፅግና ሰው ተኮር ፓርቲ ስንል በተጨባጭ በሁሉም መልኩ ከወገናችን ጎን መሆናችንን በማሳየት ነው ያሉ ሲሆን የእለቱ ድጋፍና ጉብኝትም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል። በተለይ አምራች የሆነው ወጣቱ ትውልድ የተቸገሩ የታመሙትን ቀርቦ በማገዝ እና በመንከባከብ ለወገን ደራሽነቱን ወርዶ ሊያሳይ ይገባል ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ትራንስፖርት ባለስልጣን እና ትራፊክ ፖሊስ የሚያደርጉትን ርብርብ በበጎ ፍቃድ ወርዶ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።
በጉብኝቱ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጎጅዎችን ወርደን በመመልከት ከጎናችሁ ነን በማለት ድጋፍ ስናደርግ ብልፅግና የህዝብ ፓርቲነቱን ለማሳየት ነው ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሹክሪ አብዱረህማን በበኩላቸዉ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከል የኛም ኃላፊነት ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያት እያደረጉ ላለው ተሳትፎ አመስግነው የእለቱ የወጣት ክንፋ ተግባር የዚሁ አንድ ማሳያ ስለመሆኑ አንስተዋል። ከቅድመ መከላከል እና ግንዛቤ ስራው ጎን ለጎን በሆስፒታል ያሉትን የማበርታቱ ተግባር በሁሉም አካላት ሊለመድ እንደሚገባ ነው የጠቆሙት።
በጉብኝቱ ከፌደራል የተጋበዙ እንግዶች እንዲሁም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከትራንስፖርትና ከትራፊክ አደጋ የተውጣጡ አካላት ተሳትፈዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ህዝብ ግንኙነት


