በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸዉ ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ገዛህኝ አዳርጌ ገለጹ

#DGC መጋቢት 16/2017

በአስተዳደሩ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በወጣቶች ክንፍ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ገዛህኝ አዳርጌ የተመራው የብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ አባላት፤ እንዲሁም በአስተዳደሩ ከሚገኙ የተለያዩ አደረጃጀቶች የተውጣጡ ወጣቶች እየተሰሩ ያሉ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጓብኝተዋል።

በጉብኝት መርሀ ግብሩም በአስተዳደሩ በራስ አቅም እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን የሲቪክ ሴንተር ፣የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም፣የኢትዮጵያ አየር ሀይል 3ኛ አየር ምድብን፣የኮሪደር ልማት እንዲሁም በብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ጊቢ ውስጥ በሌማት ቱርፋት የተከናወኑ ስራዎችን ተዘዋውረው ጓብኝተዋል።

በጉብኝቱም የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የወጣቶች ክንፍ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ገዛህኝ አዳርጌ ሲገልጹ በአ።ስተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶች የወጣቶችን ተሳትፎና ና ተጠቃሚነት ያረጋገጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብልጽግና ለማረጋገጥም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ወጣቶች በስፋት እንዲሳተፉ ማድረግ ወሳኝ መሆንና ወጣቶችም በልማቱ በንቃት ተሳታፊ ሆነው እየተገነባች የምትገኘውን አዲስቷ ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ያነጋገርናቸው በጉብኝቱ የተሳተፉ አካላትም ብልጽግና ፓርቲ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ጀምሮ በመጨረስ አዲስ የስራ ባህል ያስተዋወቀ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሰላም ለማ

ምስል ፦ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *