የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤና የጎርፍ ተጋላጭነትን መቀነስ ላይ ትኩረት ያደረገው የSUNCASA ፕሮጀክት ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑ ተገለፀ::

#DGC መጋቢት 17/2017

በድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣንና በአጋር አካላት ትብብር እየተተገበረ የሚኝው የSUNCASA ፕሮጀክት የአንድ አመት የስራ አፈፃፀም የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተገምግሟል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱ መሀመድ ፕሮጀክቶች በአንድ መህበረሰብ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ታስበው የሚከናወኑ መሆናቸውን ገልፀው የSUNCASA ፕሮጀክት ከጎርፍ ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን መሰረት አድርጎ በተለይም የደቻቱ ተፋሰስን ይዞ በጎርፍ ምክንያት የሚደርሱ ችግሮችን ለመቋቋም የሚተገበር እንደሆነ በመድረኩ ላይ ገልፀዋል ።

በግምገማ መድረኩ ፕሮጀክቱ እስካሁን ባለው ትግበራ የተገኙ ውጤቶች አሁን አየተተገበሩ ያሉ ስራዎች የተገኙ ውጤቶች ያጋጠሙ ችግሮችና ወደፊት ሊከናወኑ የሚገባቸው ጉዳዮች በስፋት መፈተሻቸውን ስራ አስካሂያጁ ተናግረዋል።

ለፕሮጀክቱ መነሻ የሆነው በደቻቱ ተፋሰስ ላይ በሃረማያ ዩነረቨርሲቲ የተከናወነው ጥናት ሲሆን የጥናቱ ውጤትም በተሳሰሱ የተለያዩ የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ከተደረገና ከሌሎች አጎራባቾች ክልሎች ጋር በቅንጅት ከተሰራ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያሳየ እንደነበር አመላክተዋል።

ፕሮጀክቱ በሃረማያ ዩኒቨርስቲ፣ ቦሃረርጌ ካቶሊክ ሴክሬተርያት እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ጋራ የሚመራ ሲሆን ሌሎች የአስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች ጋር በጋራ የሚተገበር መሆኑ ታውቋል።

የSUNCASA ፕሮጀክት በአፍሪካ ሶስት አገራት ማለትም ጁሃንስበርግ ሳውዝ አፍሪካ፣ኪጋሊ ሩዋንዳ እንዲሁም በኢትዮጵያ ድሬዳዋ ላይ በካናዳ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ ተግባራዊ እየተደረገ አንደሚገኝ አቶ አለምአቀፍ ጣሰው በወርልድ ሪሶርስ የፕሮጀክቱ የድሬዳዋ አስተባባሪ ገልፀዋል።

በፕሮጀክቱ ባለፈው አንድ አመት ከ300 ሺህ በላይ ችግኝ መተከሉን፣ ከ1000 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በተለይም ሴቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን በድሬዳዋ ያሉ የችግኝ ጣቢያዎች ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ ችግኞችን በማቅረብ ለችግኝ ይወጣ የነበረውን ወጪ ማዳን መቻሉ የገለፁት አስተባባሪው በቀጣይም በፐሮጀክቱ ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር በመሆን የተጠናከረ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የሃረርጌ ካቶሊክ ሴክረተሪያት (HCS) የSUNCASA ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መስፍን አለማየሁ እንደገለፁት በደቻቱ ተፋሰሱ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች በደን ችግኝ ተከላና እንክብካቤ፣ በጥምር ደን ልማት እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ እና እንክብካቤ የስራ እድል እንድተፈጠረላቸውና ድርጅታቸው ገቢውን ክትትል እና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደረጀ አቢቲ የተዘጋጀው የግምገማ መድረክ በፕሮጀክቱ አንድ አመት ትግበራ የታዩ ጠንካራ ስራዎችን በማጎልበት የታዩ ክፍተቶችን የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ፕሮጀክቱ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *