የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር በመንግስት ተቋማት የብልፅግና ህብረት አባላት የውይይት መድረክ እያካሄዱ ይገኛል::

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እና የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ በዛሬው እለት አካሄደዋል።

በለውጡ ሂደት ውስጥ የተሰሩ ሰው ተኮር ስራዎች፣ የተፈቱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን፣ የልማት ስራዎች ውጤታማነት እና ሌሎችንም መሰል ዝርዝር ሀሳቦችን በመድረኩ ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።

የመጋቢት ወር በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ታሪካዊ ክንውኖች የተከናወኑበት እንደሆነ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ በመግለፅ በኢትዮጵያ ራስን የመቻል ልዕልና ውሳኔ ማሳያ የሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት ታሪካዊ ወር መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ “የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *