#DGC መጋቢት 18/2017
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የፋይናንስ ተቋማትን የወንጀል ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያስችል የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ከሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት አመራሮች ጋር አካሄደ።
በዚህም በመድረኩ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በአሁኑ ጊዜ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ወንጀል መከላከል አስፈላጊ በመሆኑን በመግለፅ፤ እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር ወንጀሉን በጋራ ለመከላከልና ተጋላጭነትን ለማሶገድ በጋራ ተቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬው መድረክ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ኮሚሽነር አለሙ አያይዘውም የፋይናንስ ተቋማት ለማህበረሰቡ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ባጠቃላይ በገንዘብ ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ሰላማዊነት ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
በዚህም በገንዘብ ዝውውር ዙሪያ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ከፋይናንስ ተቋማት አመራሮች ጋር በመወያየት የጋራ የወንጀል መከላከል ስራ መሰራት እንደሚገባው ኮሚሽነር አለሙ ጠቁመዋል።
በስልጠና መድረኩ ሲሳተፉ ያነጋገርናቸው ተሳታፊዎች በበኩላቸው በውይይት መድረኩ በርካታ ጠቃሚ ሀሳቦችን ማግኘታቸውን ገልፀው፤ የፋይናንስ ተቋማት ደህንነትን ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ሙሉዓለም ደሴ


