#DGC መጋቢት 18/2017
በመድረኩም “የመጋቢታዊያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች” በሚል ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰነዱም በለውጡ በተገኙ የልማት ትሩፋቶች የተፈቱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን፣ የልማት ስራዎች ውጤታማነት እና ሌሎችንም መሰል ዝርዝር ሀሳቦች ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሄዶባቸዋል ።
የመጋቢት ወር በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ታሪካዊ ክንውኖች የተከናወኑበት እንደሆነ በመድረኩ የተገለፀ ሲሆን በኢትዮጵያ ራስን የመቻል ልዕልና ውሳኔ ማሳያ የሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት ታሪካዊ ወር መሆኑም ተጠቁሟል።
መድረኩ ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ላይ በመወያየት ለሀገራዊ ብልፅግና ስኬት እንተጋለን ሲሉ ቃል ገብተዋል።


