የአስተዳደሩ የመልካም አስተዳደር የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት አዘጋጅነት የ2017 በጀት ዓመት የተቋማትና የከተማ ወረዳዎች የለወጥ ስራዎችና የመልካም አስተደደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክቶሬቶችና የወረዳዎች የሲቪል ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ማስተባበሪያዎች በተገኙበት የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።
በመድረኩ የአስተዳደሩ የመልካም አስተዳደር:የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታ እና የከንቲባ ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ም/ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት በወረዳም ሆነ በሴክተር ተቋማት በመንግስት የአገልጋይነት ቦታ ላይ ተቀምጠው ህዝብን እንዲያገለግሉ እድሉን ያገኙ አመራርሮች እና ባለሙያዎች የተቋማቸዉን የዉስጥና የዉጪ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት የሕዝብን ፍላጎት በመረዳት በበጀት ዓመቱ ያቀዱትን የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት እንዳለባቸዉና የተገልጋይ አቤቱታና ቅሬታዎች በወቅቱ መፈታት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በእቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ የፍትሕ ፀጥታ ሕግ ጉዳዮች ቢሮ: ወጣትችና ስፖርት ኮሚሽን: ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ባለስልጣን እና ወረዳ 8 አስተዳደር ጽ/ቤት ሪፖርታቸዉን አቅርበዉ አስተያየት ተሰጥቶበት በተያያዘም የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጥናት ግምገማ ዳይሬክቶሬት
በሱፐርቪዥን ምልከታ የታዩትንና የተጠቃለለ የዘጠኝ ወር ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሞ ግብረ መልስሰ ተሰጥቶበታል።
በመጨረሻም መድረኩን የመሩት ክብርት ወ/ሮ ሰዓዳ አዋሌ በዉይይቱ መጠቃለያ ላይ ሲያስቀምጡ: በቀጣይ ሁሉም ወረዳዎችና ተቋማት በሕዝብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና የሕዝብ ቅሬታና አቤቱታዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰሩ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ሲል መረጃውን ያደረሰን የከንቲባ ጽ/ቤት ነው።


