በዚህም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት አመቱ ያከናወናቸው ተግባራት የተከናወኑ በርካታ ሥራዎች በሪፖርት አቅርቧል። የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድኑ የቀረበውን ሪፖርት ከተመለከተ በኋላ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ሚሰጡ ግብረመልሶችን በመተግበር ረገድ በአመቱ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን አንስተዋል።
የተሰሩ ስራዎችን መረጃ በአግባቡ በማደራጀት እረገድም ጥሩና ከዚህ በበለጠ እያጠናከሩ መሄድ እንደሚገባ ያስገነዘቡ ሲሆን የድጋፋዊ ክትትሉም አላማ ባለስልጣን መስሪያቤቱ በበጀት አመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት አፈፃፀም በመገምገም ግብረ መልስ ለመስጠት ያለመ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በተለይ የዘመነና የተሻለ አገልግሎት አሰጣጥን በማስፈን ረገድ አርኪ ስራ መከናወኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይም ያሉ ጠንካራ አፈጻጸሞችን አጠናክሮ በማስቀጠል ቀልጣፋ አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ በማሳሰብ በከተማ እና በገጠር ትራንስፖርት ቁጥጥር ሊጠናከር እንደሚገባም ግብረ መልስ ሰተዋል።
የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሹክሪ አብዱረህማን እና የማኔጅመንት አባላቱ የተሰጡ ግብረመልሶች ለቀጣይ ስራ አቅም እንደሚፈጥር ገልፀው በቀጣይ በዘመነና በተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ ማህበረሰቡን ለማገልገል እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።


