በዚህም በኮንፍረንሱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ፓርቲው በርካታ ፈተናዎችን በመቋቋም ውጤታማ ስራዎችን በመስራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደጉን ተናግረዋል።
የከንቲባ ጽ/ቤት እና የተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ በ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በአመራሩና በአባሉ የአስተሳሰብና የተግባር መቀራረብን ለማምጣት፣ አደረጃጀትና አሰራሮችን በጥብቅ ዲሲፒሊን ተግባራዊ በማድረግ፤ የውስጠ ፓርቲ ተግባራትን ለማጠናከር እና የዲሞክራሲ ስርዓቱን በማጎልበት የአስተዳደሩን የመልማት አቅም ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ በማድረግ እንዲሁም የማህበረሰቡን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የትኩረት አቅጣጫዎችን በመንደፍ ተግባራትን በውጤታማነት በመምራት ባለፉት አመታት የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም የፖለቲካ አቅም ግንባታ፣ የአደረጃጀት እና የህዝብ ግንኙነት ተግባራትን በማሳለጥ በተጨማሪም በንቅናቄ የሚሰሩ ተግባራት በጥብቅ ዲሲፒሊን እንዲመሩ፤ የፓርቲ እና መንግስታዊ ስራዎችን በማቀናጀት ስልታዊ አመራር በመስጠት በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻላቸውን አቶ ገበየሁ አመላክተዋል።
አቶ ገበየሁ አያይዘውም ባለፉት አመታት በተለያዩ ዘርፎች የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠልና አንዳንድ የተስተዋሉ ክፍተቶችን ደግሞ በማረም በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በብዙ ፈተና እና ውጣ ውረድ ውስጥ ታልፎ በሁሉም ኢትዮጲያውያን ርብርብ የተገነባውና አሁን ላይ በምርቃት ዋዜማ ላይ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ አቶ ገበየሁ ገልፀዋል።
በመድረኩ የከንቲባ ጽ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ህብረት 4ተኛ ኳርተር ኮንፍረንስ የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም እና ቀጣይ የ2018 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመጨረሻም ግንባር ቀደሞችን ለይቶ ማፅደቅ እንዲሁም ከብልፅግና ፓርቲ እጩ አባልነት ወደ ሙሉ አባልነት የተሸጋገሩ አባላት በመድረኩ ቃለ መሀላ የፈፀሙ ሲሆን፤ የአቋም መግለጫ ቀርቦ የእለቱ የኮንፍረንስ መድረክ ተጠናቋል።


