የናፍቆት ድሬ ሳምንት በዘንድሮው ዓመት ለአራተኛ ጊዜ መከበር ጀምሯል ።
በመጀመሪያ ቀን መርሀግብር “የናፍቆት በድሬ ፌስቲቫል” በነምበርዋን ኮሪደር ልማት ላይ በአስተዳደሩ የሚኖሩ የብሄር ብሄረሰቦች የባህል እና የወግ እቃዎች ትዕይንት እና የጣፋጭ ምግቦች ቅምሻ ተካሂዷል።
ፌስቲቫሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተገኝተው አስጀምረውታል።
ለተሳታፊዎች ስለመርሀግብሩ ገለፃ እየሰጡ እና ከጣፋጭ ምግቦቹ እያስቀመሱ ባማረ ሁኔታ ተካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ የተሳተፉት የአካባቢው ነዋሪዎች መርሀግብሩ በድሬዳዋ አስተዳደር የሚኖሩ በርካት ብሔር ብሔረሰቦችን የሚያቆራኝ እና የሚያስተሳስር መሆኑን አንስተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም መርሀግብሩ የልጅነት ትዝታዎቻቸውን የሚያስታውሱበት ድባብን እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል።
የድሬ ናፍቆት ሳምንት መርሀ ግብር በቀጣይ ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ከተለያዩ የአለም ሀገራት የመጡ ዲያስፖራዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።


