የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ አሳልፋል
የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በአስተዳደሩ እየተሰሩ ባሉ የልማት ስራዋች ፣ከክረምቱ ወር ጋር ተያይዞ ወረርሽኝ እንዳይከሰት መሰራት ስላለባቸው ስራዋች፣መሶብ የአንድ መአከል አገልግሎት እና በመሬት እና መሬት ነክ አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል
1ኛ,በዛሬው የካብኔ ስብሰባ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዋች ያሉበት ደረጃ ገምግሞ በተያዘላቸው እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቁ የክትትል እና የድጋፍ ስራው ተጠናክሮ መሰራት እንዳለበት ካብኔው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል ።
2ኛ,የክረምት ዝናብን ተከትሎ በትንኝ ንክሻ ሊከሰቱ በሚችሉ ተላላፊ በሽታዎችን በተመለከተ እና መከላከያ መንገዶቹ ላይ እንዲሁም በሽታዎችን የሚያስተላልፉ ትንኞች እንዳይራቡ በዘላቂነት ለመከላከል ከፍተኛ ካቢኔው እታች ድረስ በመውረድ ድጋፍና ክትትተል እንዲያደርጉ ውሳኔ አሳልፏል።
3,በአስተዳደሩ መሶብ የአንድ መአከል አገልግሎት ተግባራዊ ለማድረግ የማቋቋሚያ ደንቡ ላይ በመወያየት ደንቡን አፅድቋል።
4,ካብኔው በመሬት እና መሬት ነክ ጉዳይ ዙሪያ አስተዳደሩን የቱሪዝም መአከል ለማድረግ የተጠየቁ ጥያቄዋች ላይ ተወያይቶ የጋራ መግባባት በደረሰባቸው ላይ ውሳኔ አሳልፏል።
በመጨረሻ ካቢኒው በሌሎች አጀንዳዋች በመወያየት ውሳኔዋችን አሳልፏል
የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ


