በከዚራ በዲፖና በነበርዋን የተከናወኑ ከ2016 እስከ 17ዓም የታቀዱ ሶስት ፕሮጄክቶች ቢሆኑም ከእቅዱ የጸደቀውን ተተኪ ሰፈር ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ያለውን የውሃ መውረጃ ጂች ችግር እና የጎርፍ አደጋ ስጋት ተጋላጭነትን ለመቅረፍ የተሰራው ስራ ዘጠና አምስት ከመቶ በላይ የደረሰና የህብረተሰቡን ችግር ማቃለል የተቻለበት መሆኑ ተጠቅሷል።
በ2017 ዓም የታቀዱ ፕሮጄክቶች በበጀት እጥረት ሳቢያ ሳይጸድቁና ሳይከናወኑ መቅረታቸውም ለህብረተሰቡ በቀረበው ሪፖርት ላይ ተጠቅሷል።
በ2017 ዓም በዲፖ የህጻናት መጫወቻ ግንባታ፣ በነምበርዋን ለአቅመ ደካሞች የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታና ፣ ማሪያም ሰፈር ከፍተኛ ችግር የሆነውን የሴፕቲክ ታንከር ግንባታዎች የታቀዱ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክቶች ናቸው።
እነዚህን በስኬት ለማከናወን የህብረተሰብ ተሳትፎ ሀብት አሰባሰብ ስራ መከናወን ያለበት ቢሆንም የተጠበቀውን ያህል አለመሆኑ ተጠቁሟል። ይህን ለመቅረፍ ሌሎች አካባቢ ላይ እንዳለው ልምድ የህብረተሰብ ድርሻ ስልሳ ከመቶ ሲሆን መንግስት ቀሪውን አርባ ከመቶ የሚሸፍን ሲሆን የድሬዳዋ በአንጻሩ የህብረተሰቡ ድርሻ አርባ ከመቶ መሆኑም እንደ ችግር ተጠቅሷል።
መድረኩ በ2018ዓ/ም የሚከናወኑ የህብረተሰብ ልማት ተሳትፎ አብይ ኮሜቴ አባላትን በመምረጥ ተጠናቋል።


