“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ እንደራሴዎች እና በስሩ ካሉ ተጠሪ ተቋማቶች ጋር በጋራ በመሆን የክረምት የበጎ ስራ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብርን አከናወኗል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን በመርሃግብሩ ላይ እንደተናገሩት ድሬዳዋ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላት ፣ ከፍተኛ የጎርፍ ተጋላጭነት እና የአፈር መሸርሸር ስጋት ያለባት መሆኗን አስታውሰው ባለፉት ስድስት ዓመታት በዙሪያዋ በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየታዩ እንደሆነ ገልፀዋል።
ዛሬ ላይ በአረንጓዴ አሻራ ስራዎች ከሚተከሉት ችግኞች መካከል 85 በመቶ የሚሆኑት ችግኞች ለምግብነት የሚውሉ ፣ ሙቀት የሚቋቋሙ እና የውሃ እጥረት የሚችሉ በመሆናቸው ከተረጂነት ለመውጣትና ራስን በምግብ ለመቻል አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር እንደራሴ የሆኑት ዶ/ር ቢፍቱ መሀመድ እና አቶ አብዱልጃዋድ መሀመድ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት አቶ አብዲ መሀመድ ፣ የአስተዳደሩ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ነጂብ ኢድሪስ ፣ የአስተዳደሩ ዋና ኦዲተር ወ/ሮ ፋኪያ መሃመድን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማቶቹ ሰራተኞች ተገኝተዋል።


