በኢትዮጵያ የብስክሌት ስፖርት ውድድር ታሪክ ውስጥ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የጥሎ ማለፍ የታዳጊዎች ውድድር በድሬዳዋ ተከናወነ
የፈናን ፔይ የብስክሌት ሻምፒዮና የጥሎ ማለፍ ጫወታ አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ባጠናቀቁት በአቤኔዘር አለሙና እና ኢሳኮር ፍሬው መካከል የታየው ፉክክር በስፍራው ከታደመው የስፖርት አፍቃሪ እና ተመልካች ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል። አርባ ሁለት ዙሮችን በሚሸፍነውና በያንዳንዱ ዙር መጨረሻ የሆነ ተወዳዳሪ ከጫወታ ውጪ እየሆነ የመጨረሻዎቹ ሁለት ተወዳዳሪዎች እስኪቀሩ ድረስ ጠንካራ ፣ አጓጊና ብርቱ ፉክክር በታየበት በዚህ በአራተኛው ቀን የፈናን…


