በዚህም የኢንደስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍስሀ ይታገሱ በአሰሊሶ ክላስተር ገደንሰር ገጠር ቀበሌ እንዲሁም በአሰሊሶ ገጠር ቀበሌ የአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታን አስጀምረዋል።
የኢንደስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍስሀ ይታገሱ በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች አቅመ ደካማ ወገኖችን የማገዝ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው፤ቤቶቹ በ 2 ሚሊየን ብር ወጪ እንደሚገነቡ እና በአንድ ወር ውስጥ ተጠናቀው ለባለቤቶቹ እንደሚሰጡም አመላክተዋል።
በቀጣይም ባለሀብቶችን በማስተባበር አቅመ ደካማ ወገኖችን የመደገፍ ስራ በስፋት እንደሚሰራ ዶ/ር ፍስሀ አመላክተው በአረንጓዴ አሻራ መርሃ- ግብር የችግኝ ተከላ መከናወኑንም ተናግረዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤ ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን በበኩላቸው የኢንደስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በክረምት በጎ ፍቃድ እያከናወነ ለሚገኘው ተግባራት አመስግነው አቅመ ደካማ ወገኖችን በርብርብ በመስራት ማገዝ እንደሚገባ ገልፀው፤ በዛሬው ዕለት የተተከሉትን ችግኞችም መንከባከብ እንደሚገባ አመላክተዋል።
የቤት ግንባታው የሚከናወንላቸው እናት መይሙና አህመድ እና እናት ራቲያ ሀሚዳ በበኩላቸው የሚኖሩበት ቤት የማይመችና ዝናብ፣ ፀሀይና አቧራ የሚያስገባ መሆኑን በመናገር፤ አሁን ላይ አዲስ ቤት ሊገነባላቸው በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል።


