ፓስተር ዮሀንስ ኦላና እና ቤተሰቦቹ ከድሬዳዋ አስተዳደር እና ከዲያስፖራ ማህበር ጋር በመተባበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

ፓስተር ዮሀንስ ኦላና እና ቤተሰቦቹ የምስራቅ መካከለኛው አፍሪካ ከሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ዋና የፋይናስ አስተዳዳሪ( CFO) ከድሬዳዋ አስተዳደር እና ከዲያስፖራ ማህበር ጋር በመተባበር የገጠር ሴት ተማሪዎች ሆስቴል ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዳያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ቢኒያም ግርማ እንደተናገሩት መንግስት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና የአካባቢ ደኅንነትን ለመጠበቅ የሚያስችል የአረንጓዴ አሻራ ልማት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን እና በዚህም ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል።

የዲያስፖራው ማህበረሰብም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በሚደረገውን ጥረትም ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው እለትም ፓስተር ዮሀንስ ኦላና እና ቤተሰቦቹ የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ያስችል ዘንድ የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩም ለምግብነት የሚውሉ አትክልት ና ፍራፍሬ እንዲሁም የቡና ችግኞች ተተክለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *