በድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የገጠር ልማት ሴፍቲኔት በአምስት ምእራፍ የተሰሩ ስራዎች ዙሪያ የሚመክር ውይይት እንዲሁም የልምድ ልውውጥ በዛሬው እለት ተካሂዷል ። በምግብ ዋስትና ፕሮግራም በተለይም በአትክልት እና ፍራፍሬ ፣ በእንስሳት ሀብት ፣ በወተት ሀብት ፣ በአፈር እና ውሀ ጥበቃ ስራ በርካታ ስርልዎች መሰራታቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አሚን ተናግረዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ\ሮ ሚስራ አብደላ በበኩላቸው ባላፍት አመታት በግብርናው መስክ በተሰሩት ውጤታማ ስራዎች ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ከመቻሉም በላይ የእርሶ እና አርብቶ አደሩን ኑሮ ማሻሽል መቻሉንም ተናግረዋል ።
ባለፍት አመታት በድሬዳዋ አስተዳደር በምግብ ዋስትና የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የኢ.ፌ.ድ.ሪ ግብርና ሚኒስቴር የምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ\ሮ ስንታየው ደምሴ ተናግረው ፅህፈት ቤቱም በአስተዳደሩ በምግብ ዋስትና ላይ እየተሰሩ ላሉት ስራዎች በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ነው ያስታወቁት ።
የሴፍቲኔት ፕሮግራም በተለይም ነዋሪውን ህብረተሰብ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ማሸጋገር የቻለ ፕሮግራም መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የገጠር ምግብ ዋስትና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንዲሽ ባሻ ተናግረው ለፕሮግራሙ መሳካታ ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ተቋማት እና የተለያዩ ግለሰቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


