ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈን የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

የድሬዳዋ አስተዳደር አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሸን ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈን በሚስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ለከፍተኛ አመራር ለሚዲያ ባለሞያዎች እና ለዘርፉ ሙያተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው በዋናነት ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ለመከላከልና መልሶ ለማቋቀም የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት በራስ አቅም ለመሸፈን ዓላማ ያደረገ ነው ።

የድሬዳዋ አስተዳደር አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሸን ኮሚሸነር ሱሌማን አሊ በዚህ ወቅት እንደገለጹት መንግስት ተረጂነትን ለማስቀረትና የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ የልማት ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል።

የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን “ሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈን እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት የተረጂነት አስተሳሰብንና ተግባርን የሚያስቀሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በዚህም ኮሚሽኑ ሰብዓዊ ድጋፍን አደጋን ለመከላከል እና በራስ አቅም የመሸፈን ሀገራዊ ግብን ለማሳካት በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ከህብረተሰቡ እና ከመንግስት 51ሚሊዮን ሀብት በገንዘብ እና በአይነት መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ አያይዘውም ህብረተሰብ እርስ በእርስ የመረዳዳት እና የመደጋገፍ ባህልን አጠናክሮ ሊያስቅጥል እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *