የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የክልል እና ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የጋራ የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ከተማ እያካሄደ ሲገኝ፤ በመድረኩ ለመሳተፍ ወደ ድሬዳዋ ለመጡ እንግዶች የድሬዳዋ አስተዳደር የፍቅር መግለጫ ስጦታ አበርክቷል።
በዚህም ስጦታውን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ድሬዳዋ የአብሮነት፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ከተማ መሆኗን ገልፀው፤ የተበረከተው ስጦታም እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ፍቅርን ለመግለፅ መሆኑን ተናግረው።
አቶ ኢብራሂም አያይዘውም ድሬ የጀመረችውን የዲጂታል ጉዞ ለማፋጠን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተው፤ በቀጣይም በቴክኖሎጂው እውቀት ያላቸው ወጣቶችን የማፍራት ስራ በተጠናከረ መልኩ የመስራቱ ሂደት እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው “ድሬ የእንግዳ ተቀባይ ከተማ መሆኗን በተግባር አይተናል” በማለት የተናገሩ ሲሆን፤ ለተደረገላቸው ማራኪ አቀባበል አመስግነዋል።
ድሬ በከፍተኛ የልማት ግስጋሴ ላይ እንደምትገኝ ሚንስትሩ ገልፀው፤ በተለይም በቴክኖሎጂው ዘርፍ የተጀመሩ አበረታች ስራዎችን በቀጣይም ለማስፋት በቅንጅት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።


