የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ከሀምሌ ወር ግብር ከፋዮች ለመሰብሰብ ካቀደው ዕቅድ 90 ፐርሰን ማሳካት ማቻሉን አስታወቀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ከገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳሪክተር አቶ አብዱሰለም መሀመድ የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ከሀምሌ ወር ግብር ከፋዮች ለመሰብሰብ ካቀደው ዕቅድ 90 ፐርሰን ማሳካት መቻሉን በሰጡት ጋዜጣዊ መቅለጫ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የመፈፀም አቅሙ እና አገልግሎት አሰጣጡ በላቀ ደረጃ እየጨመረ እንደሚገኝ አቶ አብዱሰላም ተናግረው፤ ተቋሙ የዘንድሮ የሀምሌ ወር የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮችን ከሀምሌ 1 እስከ ሀምሌ 30 እንዳስተናገደ እና በዚህም የሀምሌ ግብር ከፋዮች በከፍተኛ ደረጃ ያለባቸውን እዳ በወቅቱ የከፈሉበት መሆኑን በማመላከት ለዚህም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አቶ አብዱሰላም አያይዘውም ተቋሙ በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የታገዙ አሰራሮችን እየተከተለ እንደሚገኝ ተናግረው፤ ከ4 ሺ በላይ የሚሆኑ ግብር ከፋዮች በቴሌ ብር ግብራቸውን መክፈል የቻሉበት መሆኑንም ገልፀዋል። በዚህም ከ 27 ሚሊየን ብር በላይ መከፈሉን አብራርተዋል።

በቀጣይም ይህ አሰራር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ግብር ከፋዩ ካለበት ሆኖ ጊዜና ጉልበቱን ቆጡቦ ያለበትን ግብር እንዲከፍል ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰሩ አቶ አብዱሰላም ጠቁመዋል።

በመጨረሻም ከሀምሌ 1 እስከ ጷግሜ 5 ደረጃ ለ ከሀምሌ 1 እስከ ጥቅምት 30 ደግሞ ደረጃ ሀ ግብራቸውን የሚከፍሉ ወቅት መሆኑን አቶ አብዱሰላም ጠቅሰው ደረጃ ለ እና ሀ ግብር ከፋዮች በተቀመጠው ጊዜ መሰረት ግብራቸውን በመክፈል ካላስፈላጊ ቅጣት እና እንግልት እንዲርቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *