ይኽ የኮሪደር ሥራ ሰፋፊ የተሽከርካሪ መንገዶችን፣ ከጎሮ እስከ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ መንገድ እንዲሁም በአካባቢው ሰፊ የወንዝ ልማትን ያካተተ ነው። ሰባት የስፖርት ማዕከላት፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና አውቶቡስ መናኸሪያዎች፣ ካፌዎች፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች የተካተቱበት ነው። እነኚህ ግንባታዎች ሥራ ፈጥረዋል፣ መገናኛ እና መዳረሻዎችን አስፋፍተዋል፣ የከተማዋን መሠረተ ልማት አጠናክረዋል።
በሁሉም መስክ ኢትዮጵያ መበርታቷን ቀጥላለች። ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ አይደናቀፍም። አይቆምም። የእነኚህ ሥራዎች ስኬት ይኽንን ያስቻለውን የተለወጠ ርዕይ እና የሥራ ባሕል ያንፀባርቃል። እስከአሁን የከተማዋ ግማሽ ያህል የተለወጠ ሲሆን የበለጠ ለማሻሻል የምንተጋባቸው ከባቢዎች አሁንም ይቀራሉ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)


