ታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ በድል በመጠናቀቁ በከፍተኛ ሁኔታ መደሰታቸውን የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
ግድቡ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ርብርብ ተገንብቶ ለውጤት መብቃቱን ነዋሪዎቹ ገልፀው፤ እኛ ኢትዮጲያኖች በጋራ በመቆም ሁሉን ማሳካት እንደምንችል ማሳያ ነውም በማለት ተናግረዋል።
ግድቡ ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላ አፍሪካውያን ኩራት መሆኑን የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ፤ ግድቡ እኛ ኢትዮጵያኖች በራሳችን ጥረት የተራሳችንን ሀብት መመስረት የምንችልበትን ትልቅ ምዕራፍ የገለጠ ነው ሲሉም ገልፀዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ አያይዘውም ግድቡ አንድነታችንን ከመቼውም በላይ ያጠናከረና የኢትዮጲያን ከፍታ ያሳየ እንደሆነ ጠቅሰው የአንድነት፣ የፅናት እና የመተባበር ውጤት እንደሆነም አመላክተዋል።


