የኮሪደር ልማቱ ድሬዳዋን ለስራና ለኑሮ ተመራጭ አድርጓታል – ነዋሪዎች
የኮሪደር ልማቱ ድሬዳዋ ከተማን ለስራና ለኑሮ ተመራጭ አድርጓታል ሲሉ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ። በከተማዋ በመጀመሪያው ምዕራፍ የተገነባው ከ11 ኪሎ ሜትር በላይ የኮሪደር ልማት ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል። የተገነባውን የኮሪደር ልማት አስመልክተው አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፤ የኮሪደር ልማቱ የድሬዳዋን ገፅታና ውበት በመጨመር ከተማዋን ለስራና ለኑሮ ተመራጭ አድርጓታል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ሸምሸዲን ፀጋዬ እንደገለፁት፤ የኮሪደር ልማት በከተማዋ አንዳንድ…


