በዚህም በጉብኝቱ የማዕከሉ ዋና አስተባባሪ አቶ አወቀ ለገሰ ስለማዕከሉ አጠቃላይ የስራ እቅስቃሴ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰተዋል።
ክብርት ሚኒስትሯ ድሬ መሶብ በርካታ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ ዜጎችን በሚመጥን መልኩ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ሚኒስትሯ ድሬ መሶብ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በዜጎች ላይ ይፈጠር የነበረውን የጊዜ እና የጉልበት ብክነት በመቀነስ እርካታቸውን እንደሚያሳድግም አመላክተዋል።
በመጨረሻም ሚኒስትሯ የድሬዳዋን የልማት ግስጋሴ በማድነቅ በተለይም አሰራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረጉ ረገድ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።


