የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስፖርት ክለብ ከታን ኢንጂ ነሪንግ እና ትሬዲንግ ጋር ለ 3 አመት የሚቆይ የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተፈራርሟል::

በፊርማ ስነ-ስረአቱ ላይ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋችና የታን ኢንጂነሪግ እና ትሬዲንግ ስራ አስኪሀጅ አቶ ስፉአድ ኢብራሂም ድሬዳዋ ተወልጄ ያደኩበት እንደመሆኑ የድሬደዋ እግርኳስ ስፖርት ክለብን በዚህ መልኩ በስፖንሰር ሺፕ ድጋፍ ለማድረግ በመቻሌ ደስታ ይሰማኛል ሲል ገለጿል።

ክለቡ በእግርኳስ መድረክ ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆን ቀጣይነት ያለው ሌሎች ድጋፍችንም ለማድረግ ድርጅታቸው ዝግጁ መሆኑን አመላክተዋል።

የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅና የድሬደዋ ከነማ እግርኳስ ስፖረት ክለብ ቦርደ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም ክለቡ ህዝባዎ እንዲሆንና የድሬዳዋ ተወላጅና ወዳጆች መሰረቱ እንዲሆን በደንብና በአሰራር የታገዘ ቀጣይነት ያው ስራ ለማከናወን እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የስፖንሰር ሺፕ ምንጮችን ማሳደግ እና ህዛባዊ መሰረትን ማስፋት የክለቡን ገቢ ከፍ በማድረግ እራሱን ችሎ እንዲቆም ያስችለዋልም ሲሉ ኢንጂነር ጀማለ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ በ2017 ዓ.ም የነበሩ የክለቡን ጠንካራ ጎኖች አስቀጥሎ ማስቀጠል እንደሚገባና ድሬዳዋን በእግር ኳሱ ያላትን መልካም ስም መመለስ በሚቻልበት መልኩ የክለቡ አመራሮች አሰልጠኞችና ተጫዋቾች ከህዝቡ ጋር በመሆን መስራት ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ድሬዳዋ የበርካታ ስፖርተኞች መፍለቂያ መሆኖን አሁንም ታዳጊዎች ላይ አጠንክሮ በመስራት ለዋናው ቡድን ግብአት የሚሆኑ ተጫዎችን ማፍራት እንደሚገባም ወ/ሮ ሙሉካ ጠቁመዋል።

የታን ኢንጂ ነሪንግ እና ትሬዲንግ ከዚህ በፊት የድሬዳዋ ስታዲየም ደረጃውን የጠበቀ አለም አቀፍ ሜዳ እንዲሆን ግንባታውን ያከናወነና አሁን ላይም የሃላባ ስቴዲየምን በተመሳሳይ መልኩ ግንባታ እያከናወነ የሚገኝ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *