የሚዲያ አጠቃቀምን በማዘመን ገዢ ትርክትን ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት በየደረጃው ያለው አመራርና አባል ሚና ወሳኝ ነዉ ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኢፍቱ መሀመድ ገለፁ

በብልጽግና ፓርቲ ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ከሴቶች ክንፍ ከተቋማት ና ከወረዳዎች ለተውጣጡ ለግንባር ቀደም አመራር እና አባላት በሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጥቷ።

በመድረኩም በብልጽግና ፓርቲ ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ኢፍቱ መሀመድ በንግግራቸው የሚዲያ አጠቃቀምን በማዘመን በእውነት እና በእውቀት ላይ የተመሰረተ የሚዲያ እና የተግባቦት ተግባራትን ለመፍጠር በየደረጃው ያለው አመራር ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

አመራሩና የሚዲያ ሰራዊት ሁሉንም የሚዲያ አማራጮችን በተገቢው በመጠቀም የፓርቲውን ፓሊስና አጀንዳ በማሳለጥ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንዳለበት ገልጸዋል።

ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት በሚደረገው ሂደት የተደራጀና የተቀናጀ የሚዲያ አጠቃቀም ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑንም ሃላፊዋ ወ/ሮ ኢፍቱ ጠቁመዋል።

በመድረኩም የሚዲያ አጠቃቀም የሚዲያ ሰራዊት ለውጤታማ ዲጂታል ተሳትፎ በሚል የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ጠንካራ የሚዲያ ሰራዊት በመፍጠር ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት ሚዲያ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀጣይ የሚዲያ አጠቃቀምን በማዘመን ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *