በአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund) ፕሮጀክት በድሬዳዋ እና በሀረር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸን የፕሮጀክቱ የሴክሬተሪያት ቡድን አባላት ገለፁ::

የአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund) ፕሮጀክት የሴክሬተሪያት ቡድን አባላት በድሬዳዋ እና በሀረር በፕሮጀክቱ የተሰሩ ስራዎችን በመጎብኘት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም የእርስ በእርስ ግንኙነቱን በሚያጠናክሩ እና ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ በሚገኝበት ሀሳቦች ዙሪያ መክረዋል።

በውይይት መድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና፣ ዉሃ፣ መአድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ በመስክ በፕሮጀክቱ ከንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የተቆፈሩ ጥልቅ ጉድጓዶችን፣ የመስመር ዝርጋታ ስራን፣ የውሃ ቦኖዎችን እና በአጠቃላይም ለመስኖ ስራ የሚውሉ የውሃ ማቆሪያዎችን መመልከታቸውን ገልፀዋል።

የፕሮጀክቱ የሴክሬተሪያት ቡድን አባላት በበኩላቸው በተመለከቱአቸው ስራዎች መደሰታቸውን ገልፀው፤በአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund) ፕሮጀክት በድሬዳዋ እና በሀረር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸው ገልፀዋል።

አባላቱ በቀጣይም ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ በጋራ እንደሚሰሩ አመላክተዋል።

የፕሮጀክቱ አስተባሪ አቶ ሚኪያስ ስሜ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በ22 ወረዳዎች እና በ10 ክልሎች እየተተገበረ እንደሚገኝ ገልፀው ድሬዳዋም ተጠቃሚ መሆኗን ጠቅሰዋል።

በመጨረሻም ለእንግዶቹ የድሬዳዋን ባህል የሚገልፅ አልባሳት ስጦታ ተበርክቷል።

የአረንጓዴ አየር ንብረት ፈንድ (Green Climate Fund) እ.አ.አ በ2010 የተቋቋመ ሲሆን ዋና መቀመጫውን በኮሪያ ሪፐብሊክ ሶንድጎ አድርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *