በመርሀ ግብሩ ለተለያዩ አሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ አስከፊነት እና ሊደረግ በሚገባው ጥንቃቄ ላይ ተንቀሳቅሰው ግንዛቤ ፈጥረዋል።
አሁን ላይ ለበርካታ ዜጎቻችን ህልፈት ለሀገር ኢኮኖሚ ጉዳት እየሆነ የሚገኘውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የሁሉም ዜጋ ርብርብ ወሳኝ ስለመሆኑ ይጠቀሳል በአስተዳደሩ በተለያየ የሙያ መስክ በመንግስት የስራ ሀላፊነት ላይ የሚገኙ ሴት አመራሮችን እና ባለሙያዎችን ያሳተፈ የመንገድ ደህንነት የንቅናቄ መርሀግብር በብልፅግና ፓርቲ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአስተዳደር ዘርፍ የሴቶች ክንፍ አባላት ከድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት ተካሂዷል።
በስነ-ስረአቱ ላይ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሹክሪ አብዱረህማን እንደተናገሩት አባላቱ በእለቱ ያከናወኑት ተግባር እንደባለስልጣን መስሪያቤት የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ለሚሰሩ ስረዎች ትልቅ አቅም ሚፈጥርና ለሌሎችም አርአያነት ያለው ተግባር ነው ብለዋል። በትራፊክ አደጋ በይበልጥ የቤተሰብ ምሶሶ የሆኑት ሴቶች እና ህፃናት እንደመጎዳታቸው ይህን ለአሽከርካሪዎች ግንዛቤ መፈጠሩ አደጋን ለመከላከል ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል መሰል ቅንጅታዊ ስራዎች በቀጣይም እንዲጠናከሩ ጥሪ በማቅረብ።
በብልፅግና ፓርቲ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኢፍቱ አህመድ በበኩላቸው መርሀግብሩ በአስተዳደር ደረጃ እየተካሄደ ካለው “በጎነት ለኢትዮጵያ” አስራ አንድ የትኩረት መስኮች አንዱ የመንገድ ደህነንት ላይ ግንዛቤን መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል። በእለቱም ሴት የቤተሰብ ማገር እንደ መሆኗ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ እርሷን ጨምሮ ቤተሰቧ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስቀድሞ ለመከላከል በተለይ አሽከርካሪው ሰፊ ኃላፊነት ስላለበት ለዚህም ግንዛቤ ለመስጠት መንቀሳቀሳቸውን ገልፀዋል።
ያነጋገርናቸው ሴት አመራሮችም ከእለቱ መርሀ ግብር ባለፈ በየተቋማቸው መሰል ግንዛቤዎችን በስፋት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በመርሀግብሩ ለተለያዩ አሽከርካሪዎች ውሀና ቴምር በማደል በመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ አስከፊነት እና ሊደረግ በሚገባው ጥንቃቄ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራን ሰርተዋል።


