“የኦሮሞ የምስጋና ስርዓት ደምቆ የሚታይበት ይህን ታላቅ በዓል ስናከብር፥ የኢሬቻ ዋነኛ እሴት የሆኑትን ሰላም፥ ምህረት እና አንድነትን አጥብቀን መያዝ ይገባናል።” – የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለ2018 ዓ.ም ኢሬቻ መልካ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለ2018 ዓ.ም ኢሬቻ በዓልን አስመልክተው በትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንደገለፁት “የኦሮሞ የምስጋና ስርዓት ደምቆ የሚታይበት ይህን ታላቅ በዓል ስናከብር፥ የኢሬቻ ዋነኛ እሴት የሆኑትን ሰላም፥ ምህረት እና አንድነትን አጥብቀን መያዝ ይገባናል።” ብለዋል።

ከንቲባው በመልዕክታቸው አክለውም “በቀጣይ የአስተዳደራችንን ብሎም የአገራችን ኢትዮጵያን ማንሠራራት የሚያረጋግጡ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንድንችል፥ ፈተናዎችን ሁሉ ተቋቁመን በበለጠ ትጋት ልንሠራ ይገባናል” በማለትም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *