የድሬዳዋ ከተማ ዋንጫ/ድሬዳዋ ሲቲ ካፕ የእግር ኳስ ጨዋታ የመክፈቻ ጨዋታው በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ድሬ ከነማ እና በጅቡቲ ሪፓብሊካን መካከል በተካሄደ ጨዋታ ተጀምሯል።
ለወራት ሲጠበቅ የነበረው “የድሬዳዋ ከተማ ዋንጫ” / “ድሬዳዋ ሲቲ ካፕ” የእግር ኳስ ውድድር ዛሬ ከሰዓት በኋላ 11:00 ላይ የመክፈቻ ጨዋታው በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በአስተናጋጁ ከተማ ክለብ ድሬ ከነማ እና በጅቡቲ ሪፓብሊካን መካከል በተካሄደ ጨዋታ የተጀመረ ሲሆን፣ የመከፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የካቢኔ አባላት፣የውድድሩ አዘጋጆችና አሰልጣኞች እንዲሁም የድሬዳዋ እግር ኳስ ወዳድ የስፖርት ቤተሰቦችና ደጋፊዎች በስታዲየሙ ተገኝተው ጨዋታውን ተከታትለዋል።
ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ተገልጿል። አምስት ክለቦችን የሚያሳትፈው ይህ ውድድር በድሬዳዋ ከተማ ለእግር ኳስ አፍቃሪዎች ደስታን እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በአስተናጋጁ ከተማ ክለብ ድሬ ከነማ እና በጅቡቲ ሪፓብሊካን መካከል በተካሄደው ጨዋታ በተጀመረው በድሬዳዋ ከተማ ዋንጫ/በድሬዳዋ ሲቲ ካፕ ጨዋታ የመከፈቻ መርሃ ግብር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና የካቢኔ አባላት፣የውድድሩ አዘጋጆችና አሰልጣኞች እንዲሁም የድሬዳዋ እግር ኳስ ወዳድ የስፖርት ቤተሰቦችና ደጋፊዎች በስታዲየሙ ተገኝተው ጨዋታውን አስጀምረዋል።
በመክፈቻ ጨዋታው በአስተናጋጁ ከተማ ክለብ ድሬ ከነማ እና በጅቡቲ ሪፓብሊካን መካከል በተካሄደ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ የድሬ ካፕ የመጀመሪያ ጫዋታውን በድል ጀምሯል።
ጠንካራ ፉክክር በታየበት የመክፈቻ ጫወታ ድሬዳዋ ከተማ መሐመድኑር ናስር እና ያሬድ ታደሰ ባስቆጠሩት ግሩም ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፏል።
በእለቱ ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረውና ለድሬዳዋ ከተማ ሁለተኛ ጎል ያስቆጠረው ያሬድ ታደሰ የጫወታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
የድሬዳዋ ከተማ ዋንጫ ቀጣይ ጨዋታ ነገ ቅዳሜ መስከረም 24 ከቀኑ 10:00 ላይ
ድሬ ምርጥ ከ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሚያደርጉት ጨዋታ ቀጥሎ እንደሚካሄድ የውድድሩ መርሀግብር ያስረዳል።
በድሬዳዋ የሚካሄደው ይህ ሲቲ ካፕ፣ የአካባቢውን እግር ኳስ ለማነቃቃት ብቻ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ እና በጎረቤት ጅቡቲ ክለቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነት እና የስፖርት ትስስር ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።


