ቀጣዩ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒ እንዲሆን ይሠራል – ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ

በቀጣይ ዓመት የሚካሄደው ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተአማኒ እንዲሆን መንግሥት በኃላፊነት እንደሚሠራ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ የመንግሥት ትኩረት አቅጣጫዎች ከሆኑት ጉዳዮች መካከል ቀጣዩን ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ማድረግ እንደሆነ ጠቁመዋል።

“መላው የሀገራችን ሕዝብ ኢትዮጵያ ያቀደቻቸውን እና የጀመረቻቸውን ግዙፍ የለውጥ እርምጃዎች አበርትቶ እንዲደግፍ ጥሪ አቀርባለሁ” ያሉት ፕሬዚዳንት ታየ፣ ለተግባራዊነቱም ሕዝቡ በትጋት እንዲሳተፍ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ወዳጆችም ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ጎን ሆነው የዚሁ ስኬት አጋር እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *