ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት 8.8 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ገለጹ።
መንግሥት ኢኮኖሚውን ከዕዳ ጥገኝነት በማላቀቅ፤ በራስ አቅም ችግሮችን በመፍታት እና ወደ ራስ ቻይ አምራችነት ለማሸጋገር ባደረገው ጥረት፤ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የሀገሪቷ ኢኮኖሚ 8.8 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡንም ነው ያነሱት።
ፕሬዚዳንቱ መንግሥት የልማት አቅጣጫዎቻችን ውስን ከሆኑ ዘርፎች ወደ ተለያዩ እና በርካታ ዘርፎች ማሳደጉንም ጠቁመዋል።
የኢኮኖሚው የለውጥ መሰረቶቻችን አቅሞችን በማወቅ፣ በችግር ውስጥ ዕድል በማየት፣ በፈጠራ፣ ፍጥነት በታከለበት እንዲሁም በትብብር ዘላቂ ግቦችን ማሳካት ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የማዕድን ጥሪቶችን ወደ ሀብት ምንጭነት በመቀየር፤ የሀገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ ማስቻሉንም አንስተዋል።
የሀገሪቷን ቱሪዝም ሀብቶች ወደ ጉልህ የዕድገት ጎዳና በማሸጋገር የማኅበረሰቡን አኗኗር ለመለወጥ ብርቱ ጥረት መደረጉንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።


