6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በነገው ዕለት ይካሄዳል።
የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአንድ ዓመት የሥራ ጊዜ ከመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ መሆኑ ተደንግጓል፡፡
በዚህ መሰረትም የ6ኛው ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የተጠናቀቀ ሲሆን÷ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት በነገው ዕለት ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ በማብሰር የፌደራል መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡


