በግብርና ውሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ 5ኛው ምዕራፍ የገጠር ምርታማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የ2017 በጀት ዓመት የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም የግራንት ትራንስፈር ተጠቃሚዎች በመረጡት ገቢ ማስገኛ አማራጭ ስራ መስክ ስምሪት ትግበራን አስመልክቶ ለወረዳና ቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።
በግንዛቤ ማስጨበጫው የክብር እንግዳ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ እንዳሉት ባለፉት አመታት መንግስት እና አጋር አካላት በጥምረት በሚደረግ የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በኩል የአስተዳደሩ የገጠር የህብረተሰብ ክፍል የምግብ ፍላጎት ለማሟላት የገንዘብ እና የአህል ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል።
ከለውጡ በኋላ መንግስት ሀገራችንን ከተረጂነት ለማላቀቅ በወሰደው ቁርጠኛ አቋም መሰረት በግብርናው ዘርፍ በርካታ አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልፀው የኘሮግራሙ ተጠቃሚዎች ከተረጂነት ወጥተው በዘላቂነት የምግብ ዋስትናቸውን እንድያረጋግጡ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከፌደራል እስከ ቀበሌ ያለው የመንግስት መዋቅር በፕሮግራሙ የተያዙትን እቅዶች በስኬት በመፈፀም በፕሮግራሙ የታቀፉትን ዜጎች ወደ አምራችነት አንዲሸጋገሩ እና ከተረጂነት አንዲላቀቁ ዜጎችም የሚሰጣቸውን ድጋፍ ባግባቡ ተጠቅማችሁ እራሳችሁን ከተረጂነት ከማላቀቅ አልፎ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
የግብርና ውሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ በበኩላቸው 5ኛው ምዕራፍ የገጠር ምርታማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የመጨረሻው ዓመት በመገባደድ ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው ፕሮግራሙ በ2018 በጅት ዓመት ታህሳስ ወር ላይ የሚጠናቀቅ በመሆኑ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የድጋፍ አቅርቦት አመቻችቶ የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ አባ ወራዋች እና እማ ወራዎች በተለያዩ ገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ ተሰማርተው በጥራት አፍርተው ኑሮቸውን እንዲሻሻሉ በማስቻል እና ከፕሮግራሙ እንዲሰናበቱ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ገልፀዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ የግራንት ተጠቃሚ አባ ወራዋች እና እማ ወራዎች ቁጥር በጀት ምደባ ትርጉም ያለው ጭማሪ ተደርጎበታል ብለዋል፡፡
በበጀት አመቱ የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም ተጠቃሚ አባ እና ወራዋች እማ ወራዋች ቁጥር ወደ 6731 ከፍ ያለ ሲሆን በአስተዳደሩ ደረጃ 23 ቀበሌዎችን ተደራሽ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት በአስተዳደሩ የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ 6731የአንድ ጊዜ ጥሪት መፍጠሪያ የግራንት ትራንስፈር ድጋፍ አቅርቦት በነፍስ ወከፍ ብር 33,300 (ሰላሳ ሶስት ሺ ሶስት መቶ ብር) እንድሁም በጥቅሉ ብር 224,142,300 (ሁለት መቶ ሃያ አራት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ ሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር) ተመድቦል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት የCBE ኑር ክፍል ጋር በመተባበር በድሬዳዋ አስተዳደር በ23 ገጠር ቀበሌዎች ለሚገኙ ለ6731 የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም የግራንት ትራንስፈር ተጠቃሚ አባ ወራዋች እና እማወራዎች አካውንት ሂሳብ ቁጥር ማስክፈት ስራ ተከናውኖል የሉት ኃላፊው የግራንት ገንዘብ ስርጭት በማከናወን ወደ መረጡበት የስራ መስክ እንዲሰማሩ ለማስቻል የተዘጋጀ ኘሮግራም እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሸም በግብርና ውሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ መሃመድ አህመድ የ5ኛው ምዕራፍ የገጠር ምርታማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የ2017 በጀት ዓመት የቤተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም የግራንት ትራንስፈር ተጠቃሚዎች በመረጡት ገቢ ማስገኛ አማራጭ ስራ መስክ ስምሪት ትግበራን አስመልክቶ በተቋቋሙ አደረጃጀቶች እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የመወያያ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።ሲል የግብርና ውሀ መዓድን እና ኢነርጂ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ዘግቧል።


