ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር በተሰራው ሥራ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር በተሰራው ሥራ ውጤት ማስመዝገቡን የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሊያስ አሊዪ ገለጽ።

የብልጽግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እና በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የኮሚሽኑ መዋቅር፣ አስተዋጽኦ ላደረጉ ባለድርሻ አካላትና ግለሰቦች የእውቅና እና የምስጋና መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

በመድረኩም ኮሚሽኑ የፓርቲው የፖለቲካ ጥራት እንዲረጋገጥ፣ ሥነ-ምግባር እንዲሻሻል፣ አሰራሮች እንዲጠበቁ፣ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

በዕውቅናና ምስጋና መርሐ-ግብሩ ላይ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሰጡት በብልጽግና ፓርቲ ድ/ዳ/ቅ ጽ/ ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደረጄ ጸጋዬም በበኩላቸው የፓርቲው የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ጠንካራ ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑን አንስተው

ጠንካራ የፓርቲ መዋቅር መፍጠር የተቻለው በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ወደ ተግባር በመገባቱ ነው ብለዋል፡፡

በ2018 በጀት ዓመትም ኮሚሽኑ ጠንካራ ኢንስፔክሽን እንዲረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው አደረጃጀቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበትም ኃላፊው አሳስበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *