በድሬዳዋ ሴቶች ጓዳ ተቀምጠው ዱቄት ከመጠበቅ ይልቅ የራሳቸውን ዱቄት ፋብሪካ ከፍተው እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ

ሚኒስተሩ ይህንን የተናገሩት በዛሬው ዕለት ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ጋር በጋራ በመሆን 11 አምራች ኢንደስትሪዎችን ሲመርቁ ነው።

ከተመረቁት ኢንደስትሪዎች መካከል “ባህር ዱቄት ፋብሪካ” አንዱ ሲሆን የፋብሪካው ባለቤት እና ስራ አስኪያጅም ማርያ ሳላ ይባላሉ።

ባህር የዱቄት ፋብሪካ በ 37 ሚሊየን ብር ካታል እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ፋብሪካ ሲሆን ለ 21 ዜጎችም የስራ እድልን ፈጥሯል።

የፋብሪካው ባለቤት ማሪያ ሳላ የዛሬ ቀን ላይ ለመድረስ በርካታ ውጣ ውረዶችን እንዳለፈች በመግለፅ ፍብሪካው በመመረቁ የተሰማትን ከፍተኛ ደስታ ገልፃለች።

ድሬዳዋ 24 ሰአት የሚሰራበት የኢንደስትሪ ከተማ መሆኑን የተናገረችው እንስቷ በዘርፉ ለመሰማራት ፆታ አይገድብም የማያስፈልገው ጥንካሬ ብቻ ነው በማለት ተናግራለች።

እንስቷ የወደፊት እቅድ የምግብ ኮንፕሌክስ መክፈት መሆኑን ያመላከተች ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ ላደረገላት ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናዋን አቅርባለች።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ጓዳ ተቀምጠው ዱቄት ከመጠበቅ ይልቅ የራሳቸውን ዱቄት ፋብሪካ ከፍተው እየሰሩ ይገኛሉ ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ይህም ለሌሎች አካባቢዎችም በተሞክሮነት ሊወሰድ የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት ከተመረቀው ባህር ዱቄት ፋብሪካ በተጨማሪ ሌሎችም የዱቄት ፋብሪካዎች በድምቀት ተመርቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *