ወጣቱ ራሱን በመረጃ በማብቃት በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የበኩሉን አይነተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

“በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የበቃ ዲጂታል ድሬዳዋን እውን የሚያደርግ ወጣት እንፍጠር” በሚል መሪ ሀሳብ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ወጣት ክንፍ ፅህፈት ቤት በአስተዳደሩ ለሚገኙ ወጣት ክንፍ አመራሮች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አካሄደ፡፡

ወጣቱ መንግስት የሚያከናውናቸውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዴፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎችን በንቃት በመከታተል ራሱን በመረጃ በማብቃት በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የበኩሉን አይነተኛ ሚና ሊጫወት እንደሚገባ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትል እንዲሁም የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ መድረኩን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

በተለይም ከለውጥ መንግስት ምስረታ ጀምሮ መንግስታችን ያከናወናቸውና የተገኙ ሀገራዊ ድሎችን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ማንፀባረቅ እንዲሁም በተለያዩ አፍራሽ ሀይሎች የሚነዙ ሀሰተኛ መረጃዎችን መመከት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡

በመድረኩ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን የዳሰሰ የመወያያ ሰነድ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ኃላፊ በአቶ አህመድ ሰኢድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ጥልቅ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *