የካብኔ ውሳኔ

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል

ካብኔው ዛሬ ከሰዓት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ መንግስት የመንግስት ሰራተኛውን ኑሮ ለማሻሻል ባደረገው የደሞዝ ጭማሪ እና መሬት እና መሬት ነክ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፉል

ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ መንግስት በገለፀው መሰረት ከመስከረም ወር ጀምሮ አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ በአስተዳደሩ ተፈፃሚነቱ ላይ በስፉት ተወያይቷል።

የደሞዝ እና የአበል የአከፋፈል መመሪያ በዝርዝር ለካብኔ አባላቱ በሲቪል ሰርቨስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የቀረበ ሲሆን በአፈፃፀም ሁኔታ ላይ የአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የመንግስት ሰራተኛውን ኑሮ ለማሻሻል ደሞዝ ጭማሪው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ( ዶ/ር) በተወሰደ ትልቅ እርምጃ ሰራተኛው ተረድቶ እና ተነቃቅቶ ህዝቡን በቅንነት በታማኝነት ማገልገል ወደ ሥራ መግባት እንዲሁም ሥራቸውን በአግባቡ የሚሰሩ ትጉህ ተመስጋኝ እና ተገልጋዩን ሳያጉላሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ሥራቸውን የሚከውኑ አምራች ሀይል መሆን እንደሚገባም ክቡር ከንቲባው በውይይቱ አፅኖት ሰተው ገልፀዋል።

ካብኔው በውይይቱም የአፈፃፀም ሂደቱ ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ አሳልፋል

በመጨረሻ ካቢኒው በመሬት እና መሬት ነክ አጀንዳዋች በመወያየት ውሳኔዋችን አሳልፉል

የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *