በድሬዳዋ ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከብሯል።

“ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጰያ ማንሰራራት የአዲስ ዘመን ድል ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ’” በሚል መሪ ሀሳብ ነው የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከብሯሌ።

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት እመርታዊ ስኬቶችን ያስመዘገበችበት እና የማንሰራራት የከፍታ ዘመን የጀመረችበትን የድል ብስራት በሚያስቀጥሉ ሁነቶች ታጅቦ እየተከበረ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር በከንቲባ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ በተካሄደው መርሃ-ግብር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ክብር ከንቲባ ክብር አቶ ከድር ጅሀር ፣ምክትል ከንቲባ ክብር አቶ ሀርቢ ቡህ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪው ሰኞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚከበር በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006 አንቀጽ 2 ተደንግጎ ይገኛል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *