የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን በድሬዳዋ ወረዳ 05 እና 08 የድሬዳዋ የመጀመሪያ ደረጃ እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በክረምት በጎ ፈቃድ ለአቅመ ደካሞች የገነቧቸውን ቤቶች መርቀው ለነዋሪዎቹ አስረክበዋል

ኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሐሳብ አመንጪነት የክረምት የበገጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ኑሮ ለማሻሻል ከሚከናወኑ ተግባራት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ እንዲካሔድ መደረጉ የበርካቶችን የኑሮ ጫናና ሸክም በማቅለል ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ ነው የሉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን ፣የድሬዳዋ የመጀመሪያ ደረጃ እና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በክረምት በጎ ፈቃድ ለአቅመ ደካሞች የገነቧቸውን ቤቶች መርቀው ለነዋሪዎቹ ባሰረከቡበት ወቅት ነው ።

በወረዳ ዐ5 የሚገኘውን ቤት ያስገነባው የድሬዳዋ አስተተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ነጂብ ኢድሪስ ፣ ፍርድ ቤቶ ነጻና ገለልተኛ ሆነው ሁሉም ዜጎች የተቀላጠፈና ሚዛናዊ ፍትህን እንዲያገኙ እና ሙሉ አቅም፣ ጊዜና ጉልበት ፣ እውቀትና ሀብታቸውን ለሀገር ልማትና እድገት ላይ እያደደርጉ የህግ የበላይነት የሰፈነባት ሀገር ግንባታ ሒደት ላይ ከሚጫወቱት አይተኬ ሚናቸው ባሻገር በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሀሆናቸውን ገልጸዋል።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞቸን ቤቶች የገነቡት ተቋማት ቤቱን የገነቡላቸውን አቅመ ደካማ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደ አንድ የተቋማቸው ቤተሰብ አካል በመውሰድ ኑሯቸውን ለመለወጥና ሕይወታቸውን ለማሻሻል ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በመስጠት በሚያደርጉት ጥረትና ሒደት ላይም አዎንታዊና ገንቢ ሚና እንዲኖራቸው በቤት እድሳት የተፈጠረ ትስስር እንጂ ድጋፉ በዚህ የሚያበቃ አለመሆኑን ነው ክብርት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፈቲያ አደን የገለጹት።

የቤት እድሳቱ የተደረገላቸው አቅመ ደካማ የወረዳ 05 ነዋሪ ከልጃቸው ልጅ ጋር ዘምሞ በላያቸው ላይ ከዛሬ ነገ ፈርሶ አደጋ ላይ ሊጥላቸው ስለሚችል በክረምት ወራት ዝናብ በበጋው ደግሞ ነፋስ የሰቀቀንና የስጋት እንቅልፍ አልባ ለሊቶችን እንዲያሳልፉ ያደርጋቸው እንደነበር ገልጸው ይኼን ችግሬን በመረዳት እንዲህ ያማረ ቤት ከመገንባት አልፈው የምንተኛበት ፍራሽና የመሬት ወለል ምንጣፍ ፣ የምግብ ሬሽን ድጋፍ ጨምረው ሲሰጡኝ እንግዲህ ይሔንን በምን ቃል ደስታዬንስ ሆነ ምስጋናዬን መግለጽ እችላለሁ ሲሉ በዚህ ስራ ለተሳተፉ አከላት ሁሉ እናታዊ ምርቃታቸውን ለግሰዋል ።

በክረምት በጎ ፈቃድ ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ያከናወኑት ማህበራዊ ኃላፊነትን በሙሉ ፍላጎት የመወጣት ተግባር የሚያስመሰግን ነው ያሉት አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ፈቲያ አደን ፣ በተለይ ኢትዮጵያውያን በጋራ ታላላቅ ድሎችን የተቀዳጁበት የአንድነት ተምሳሌት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማችንን ለ 18ኛ በጋራ በምናከብርበት ታላቅ ብሔራዊ ቀን የዛሬውን ግንባታቸው እንዲህ ባማረ መልኩ የተከናወኑ ቤቶችን ዛሬ ሀገር ለደረሰችበት የእድገት ደረጃ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አቅመ ደካማ የእድሜ ባለጸጋ ዜጎቻችን ማስረከባችን ያበረከቱትን አስተዋጾ እና ዉለታቸውን ሀገር እንደማትዘነጋ ማሳያ መሆን የሚችል ነው ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *