የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም እየገመገመ ነዉ

በብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ከዘርፉ አመራሮች ጋር እያካሄደ ይገኛል።

በግምገማ መድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ በፓርቲው መሪነት በሁሉም ዘርፍ የተመዘገቡ ሁለንተናዊ ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ቀጣይነት ማረጋገጥ ከሁሉም አመራር ይጠበቃል ብለዋል።

ባለፉት ሶስት ወራት ፓርቲው የመሪነት ሚናውን በብቃት በመወጣቱ ለብልጽግና ጉዞ አጋዥ አፈጻጸሞች መመዝገባቸውን አንስተው እንደ አስተዳደር የኮሪደር ልማት፣የእምርታ ቤተመጽሀፍት እና የኮንቬክሽን ሴንተር በግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች አመርቂ ስራዎች መስራታቸውን በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል።

በመድረኩ የአንደኛ እሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *