በፈረንሳይ ሌጉ ከተማ ከንቲባ ሊዮኒዳስ ሰርጅ የተመራ 11 አባላትን የያዘ ልዑካን ቡድን ከሦስት ቀን በፊት ድሬዳዋ እና የሌጉ ከተማን እህትማማችነት ለማጠናከር ድሬዳዋ መግባታቸው ይታወሳል

ድሬዳዋ እና የፈረንሳይዋ ሌጉ ከተማ እህትማማች ከተሞች ሲሆኑ በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎችም ማህበራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል።

በፈረንሳይ ለቡግ (Le Bugue) ከተማ ከንቲባ የተመራ ልዑካን ቡድን ዛሬ ማምሻውን ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን የድሬዳዋ-የኮሪደር ልማት ጎብኝተዋል ።

ሉኡካን ቡድኑም ድሬዳዋ በኮሬደር ልማት ሥራን በማስፋፋት ረገድ አስገራሚ ተግባራትን እየሰራች እንደምትገኝ የፈረንሳይዋ የሉቡግ ከተማ ከንቲባ ሰርጅ ሌዎንዳስ ገልፀዋል።

በኮሪደር ልማት ሥራዎቹ ጉብኝቱ ወቅት የልማት ሥራው አስተባባሪዎች እስካሁን በጥቅሉ ከ6.2 ኪሜ በላይ የሚረዝም የኮሪደር ልማት ሥራ እንደተሰራ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *