የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ምስራቅ መምሪያ አመራሮች በአጠቃላይ በቀጠናው ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ በድሬዳዋ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ ከውይይቱ ጎን ለጎን በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
በዚህም በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸው የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ምትኩ ዳባ በቀጠናው ዙሪያ ውይይት ከመደረጉ ጎን ለጎን በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን በተጨባጭ ወርደው መመልከታቸውን ገልፀዋል።
ኮማንደሩ አያይዘውም አስተዳደሩ እያከናወናቸው የሚገኙ የልማት ስራዎች የማህበረሰብን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ መሆናቸውን ገልፀው፤ ለወጣቶች የንባብ ባህል መዳበር ጉልህ ሚና ያለው የእምርታ ቤተ-መፅሀፍ በአጭር ጊዜ መጠናቀቁ በአስተዳደሩ ስራዎች በቅንጅት እና በርብር እንደሚሰሩ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
ለተገለልጋዮች እርካታ እና የአገልግሎት ቅልጥፍናም “መሶብ ድሬ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በአጭር ጊዜ ወደ ስራ መግባቱ የሚበረታታ መሆኑን ከማንደሩ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ኮማንደር ምትኩ በተመለከቱት የልማት ስራ መደሰታቸውን ገልፀው በቀጣይም ልማቱን ለመጠበቅ እና ለማስቀጠል የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚወጡ አመላክተዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች አበረታች እና የማህበረሰቡን ችግር አቅላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።


