ባለፉት ሰባት አመታት መንግስት የዜጎች ሁለንተናዊ ብልፅግናን እንዲረጋገጥ እያከናወነ በሚገኘው ስራ አበረታች ለውጥ እየተገኘ ነው።
የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት የኢኮኖሚ ክላስተር የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወረዳ ስር የሚገኙ አራት የመንግስት የልማት ድርጅቶች በክረምት በጎ ፈቃድ በድሬደዋ ለአቅመ ደካማ ቢተሰቦች ያስገነቧቸውን 20 ቤቶች ዛሬ መርቀው አስረክበዋል ።
የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በክላስተሩ ስር የሚገኙ የፌደራል ተቋማት በድሬደዋ የአቅመ ደካማ ቤተሰቦችን ቀጣይ ህይወት በማለምለማቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በአስተዳደሩ በ2017 የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎቶች 291 አዳዲስ ቤቶች ተገንብተው እና 281 ቤቶች ታድሰው የአቅመ ደካማ ቤተሰቦችን ኑሮና አኗኗር በመሠረታዊነት እንዲለወጥ መደረጉን ገልጸዋል ።
በቀጣይም የበጋ ወራት በአስተዳደር ደረጃ ሆነ ከፌደራል ተቋማት ጋር በመቀናጀት ና ህብረተሰቡን በማስተባበር የተሻሉ ውጤቶች ለማስመዝገብ ከወዲሁ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን በመጠቆም።
ክረምት ከበጋ እየተከናወኑ የሚገኙ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች የርስ በርስ መረዳዳትና አብሮነትን ከማጠናከር በዘለለ የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች እየፈቱ መሆናቸውንም ገልጸዋል ።
የክላስተሩ አመራርና የኢፌድሪ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት መንግስት የዜጎችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ የሚገኛቸው ተግባራት አመርቂ ውጤቶች እያመጡ ናቸው ።
እነዚህን ውጤቶች በላቀ ደረጃ በማስቀጠል የምንፈልገውን የብልፅግና ጉዞ በላቀ ፍጥነትና ጥራት የሚረጋገጠው በመንግሥት ውስን በጀት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የርስ በርስ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት ባህልን በተቀናጀ መንገድ አጠናክሮ በማስቀጠል ጭምር መሆኑን አስምረውበታል ።
ይሄን መሠረት በማድረግ በለውጡ አመታት መንግስት የበጎ በረድ አገልግሎቶች በተጠናከረ ተቋማዊ አደረጃጀት እንዲመሩ በማድረግ የማህበራዊ ና የኢኮኖሚያዊ ልማቶች በላቀ ደረጃ ማሳደግ መቻሉ የዚሁ ማረጋገጫ መሆኑን በመግለፅ ።
በዛሬው ዕለት በድሬዳዋ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወረዳ አደረጃጀት ስር በሚገኙ የልማት ተቋማት የተገነቡ ቤቶችም የአቅመ ደካማ እና የአረጋውያንን ቤተሰቦች ህይወት የሰመረ ማድረጋቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።
በመሆኑም በተገኙ ውጤቶች ሳንዘናጋ የአብሮነት እሴት በማጠናከር አካላዊና መንፈሳዊ እርካታን በሚሰጠው በዚህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚደረገውን ርብርብ ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የጀመረውን አበረታች ስራ በላቀ ደረጃ በገጠርና በከተማ ማስቀጠል እንዳለበት በመጠቆም ።
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከሶስት መቶ ሺ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ አስራ አራት አይነት የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የገለፁት ደግሞ ዘርፉን የሚያስተባብሩት የድሬደዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽነር ካሊድ መሐመድ ናቸው።
በነዚህ ልማቶች ላይ 90ሺ ወጣቶች እና የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን በማስታወስ።
ቤቶቹን መርቀው ቁልፎቹን ለባለቤቶቹ ያስረከቡት የክላስተሩ አመራር ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ፣ የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ እና ቤቶቹን የገነቡት ተቋማት አመራሮች ናቸው።


